top of page

ስለ እኛ

እነሆኝ የበጎ አድራጎት ድርጂት March 23, 2017 GC. በኢትዮጵያ፣ በአሜሪካና ካናዳ ተመስረተ::

 

እነሆኝ  የበጎ አድራጎት ድርጂት ከፖለቲካና  ከሐይማኖት ነፃ የሆነ ድርጂት ነው::

 

እነሆኝ የበጎ አድራጎት ድርጂት በኢትዮጵያ ውስጥ እረዳት አልባ ለሆኑ ሕፃናት መጠለያ፣ ምግብ ፣ ውሐ፣ ልብስ፣ህክምና እንዲሁም ከትምህርት ገበታቸው ለተፈናቀሉ ህፃናት ወደትምህርት ገበታቸው  ተመልስው  የወደፊት ሕይወታቸውን  በጥሩ ሁኔታ እንዲቀጥሉ የሚያደርግ ትርፋማ ድርጂት ነው::

JPEG image-4DCF-B1F0-60-9.jpeg

 እነሆኝ ማለት ምን ማለት ነው?

 

እነሆኝ ማለት እራስን ዝቅ አድርጎ  ለተጎዱ ወገኖቻችን  ለአገልግሎት  እራስን መስጠት፣ትህትነት ፣ ቅንነት ፣ ቸርነት ለበጎ ነገር ሁሉ ለአገልግሎት ቀርቦ ማቅረብ መሆን በፍቃደኝነት  በሙሉ ልብ መታዘዝ ::

እነሆኝ፤ ራእይ፡ተልኮው፡ውስጣዊው ዋናው አላማው ይህ ነው።

እነሆኝ፦ ራእይ።

የተራቡትን፤ መኖርያ ቤት ውይም መጠጊያ የሌላቸውን፤ በጊዜአዊ ችግር ህፃን ይዝው ተስፋ ያጡትን ህብረተስብ ከእግዚአብሔር ጋር የተኻለ ኑሮ አንዲኖሩ ዓለም አቀፍ ድረስ የሆነ ህብረተስብ መፍጠርና ማቋቋም ነው።

እነሆኝ ተልኮው

እነሆኝ ዋናው እላማው በመጠለያ በምግብ ሆነ ንፁህ ውሐ ማግኝትለማይችሉ እንዲሁም ህክምናም ለሚያስፈልጋቸው ማቅረብ ነው። በተጨማሪም ኑሮቸውን ለመግፋት ላቃታቸው በዚሁ ችግር ከትምህርት ገበታቸው ለተፈናቀሉ እና ላልጀመሩ ወጣቶች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ እና እንዲጀምሩ ማድረግና መዎለ ሕፃናት መግባት ሲገባቸው በጊዚያዊ ኑሮ አለመሳካት እድል ላላገኙ ህፃናት ይህን እድል በመስጠት የወደፊት መልካም እና ጤናማ ዜጋ ማድረግ ነው።

ውስጣዊው ዋናው አላማው ይህ ነው

1 - በህብረተስባችን (በስው) ኧምሮ ላይ ሊራሳ የማይችል መልካም ስራ ስርቶ(ጥሎ) ልመጭውም ትውልድ ጥሎ ማልፍ ነው።

2- በሐገርም ውስጥም ሆን በውጭ ሐገና እርዳታ እና ድጋፍ ያሚስጡ ድርጂትም ሆነ ግለስብ( ህብረትስብ) መፈለግ እና ማቅረብ።

3- የእነሆኝ አላማ እና ውጤት ማክበርና ማጠንከር።

4- የተችገሩትን ህፃናት እና ህብረተስብ በእነሆኝ ስም እንደ አንድ ቤተስብ ማቀፍ። እና ስብስቦ መያዝ።

5- እነሆኝ የተስጠውን የገንዘብ ገቢ በሐላፊነት በማግባት እና በማውጣት የሚስሩትን ሁሉ በትክክል በመረጃ መያዝና መቆጣጠር።

6- እያንዳንዱ የእነሆኝ አባል ሁሉ እኩል ለእነሆኝ መብትና፤ ሐላፊነት እንዲሁም ዎጋ እንዳለው እነሆኝ ያምናል ያስጠብቃል

JPEG image-4DB1-BC2D-25-11.jpeg

ድርጅታችን

በእንሆኝ፣ በምናገለግላቸው ማህበረሰቦች ውስጥ እርዳታ እና እርዳታ ለተቸገሩ ሰዎች በመስጠት ህይወት ላይ ተጽእኖ ለማድረግ ቆርጠን ተነስተናል። ሁሉም ሰው ከድህነት፣ ከእኩልነት እና ከኢፍትሃዊነት አጥር ተላቆ አርኪ ህይወት የመምራት እድል ይገባዋል ብለን እናምናለን። የእኛ ቁርጠኛ የባለሙያዎች ቡድን የምናገለግላቸውን ሰዎች እና ማህበረሰቦችን ደህንነት የሚያሻሽሉ ፕሮግራሞችን እና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ያለመታከት ይሰራል። እንዴት እንደተዋቀርን እና የቡድናችን አካል ማን እንደሆነ ለማየት የእኛን የእንሆኝን መስራቾች ገበታዎች ይመልከቱ።

ቀይ ረጅም እጅጌ ሸሚዝ የለበሰ ሰው ዬል የያዘ

የኢትዮጵያ መስራቾች ገበታ

የአሜሪካ ባንዲራዎች

ዩኤስኤ/ካናዳ መስራቾች ገበታ

እንሆኝ

እነሆኝ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው። አላማችንን ለማራመድ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚንቀሳቀሱ እንሆኝ ብሎው የቀረቡ መስራቾች እንሆኝን። የተሻለ አለም ለመፍጠር ስለምንሰራው ስራ የበለጠ ይወቁ።

bottom of page